የትሬዲንግ ማስያ

ከ Exness ኢንቨስትመንት ማስያ ጋር ፒፕሶች፣ የትርፍ ተመን፣ የመግዣ እና መሸጫ ልዩነት፣ ኮሚሽን እና የመሳሰሉትን ያስሉ። በእጅ መጠቀም የሚችሉት መሳሪያ ለትሬዲንግዎ የግብይት አቋሞች ውስብስብ ስሌቶችን በማቅለል ያግዝወታል።

የእርስዎ ትእዛዝ

ውጤቶች

የትርፍ ተመን
የመግዣ እና መሸጫ ልዩነት ወጪ³
ኮሚሽን
የሽያጭ ስዋፕ
የግዢ ስዋፕ
የፒፕ ዋጋ

ማስተባበሪያ፦ የትሬዲንግ ማስያ የሚቀርበው ለገላጭ አላማዎች ብቻ ነው። በዚህ ማስያ የቀረቡት ውጤቶቹ ለትምህርታዊ እና ግምት አላማዎች ነው እና እንደ ሙሉእ አስበውት እና የኢንቨስትመንት ውሳኔዎችን ለማድረግ አይደገፉበት። የእውነተኛ-ጊዜ ውጤቶች መታወቅ የሚችሉት በትእዛዝ አፈፃፀም ጊዜ ብቻ ነው።

የExness ትሬዲንግ ማስያን እንዴት መጠቀም እንደሚቻል

ደረጃ 1

የExness አካውንትዎን አይነት ይምረጡ እና የአካውንትዎን ሌቨሬጅ እና ምንዛሬ ይግለፁ።

ደረጃ 2

ከሚገኙት ዝርዝር ውስጥ የሚፈልጉትን የትሬዲንግ መሳሪያ ይምረጡ።

ደረጃ 3

የትሬድዎን አሀድ መጠን ይለዩ እና 'ያስሉ' የሚለውን አዝራር ጠቅ በማድረግ ወደ ማስላት ይቀጥሉ።

በተደጋጋሚ የተጠየቁ ጥያቄዎች


በአሁኑ ሰአት እርስዎ በመረጡት የአካውንት ምንዛሬ ትሬዲንግ ማስያ ላይ የሚታዩ 6 እሴቶች አሉ፦

  • የትርፍ ተመን - ይህ የግብይት አቋምን ለመክፈት አስፈላጊ መነሻ፣ ወይም ቀሪ ሂሳብ ነው።
  • የመግዣ እና መሸጫ ልዩነት ወጪ - የግብይት አቋም ሲከፍቱ የሚከፍሉት መጠን ነው። እዚህ ጋር የመግዣ እና መሸጫ ልዩነት ወጪ የሚሰላው በባለፈው የትሬዲንግ ቀን አማካኝ የመግዣ እና መሸጫ ልዩነት መሰረት ነው። የመግዣ እና መሸጫ ልዩነት በተለዋዋጭ ሁኔታ ሲለወጥ፣ በገበያ ሁኔታዎች መሰረት፣ የመጨረሻው የመግዣ እና መሸጫ ልዩነት ወጪ ሊለይ የሚችለው የግብይት አቋም በሚከፈትበት ወቅት ብቻ ነው። ስለ Exness የመግዣ እና መሸጫ ልዩነቶች በትሬዲንግ አካውንትዎች ክፍል በትሬድ ማድረግ የሚፈልጉት ገበያዎች ድረገጾች ላይ የበለጠ ይወቁ።³
  • ኮሚሽን - ኮሚሽን በRaw Spread እና በዜሮ አካውንትዎች ለትሬዲንግ የሚከፈል ክፍያ ነው። የሚታይዎት የኮሚሸን መጠን የትሬድ በተደረጉ አሀዶች ላይ እና ለሁለቱም የተከፈቱ እና ለተዘጉ የግብይት አቋሞች ተግባራዊ ይሆናል። የስሌት ውጤቶች ላይ የሚታይዎት የኮሚሸን በጠን የሁለቱም በኩል አጠቃላይ ክፍያ ነው (ክፍት እና ዝግ)፣ የሚከፍሉት የግብይት አቋሙን ሲከፍቱት ነው። የኮሚሽኑ ክፍያዎች ለእያንዳንዱ ትዕዛዝ እንደ የተለየ ወጪ ሲታዩ፣ በትሬዲንግ መተግበሪያ መድረኩ ላይ የትእዛዙ ትርፍ እና ኪሳራ ስሌት ላይ የመግዣ እና መሸጫ ልዩነቶች እንደተጠቃለለበት ልብ ሊባል የሚገባ ጉዳይ ነው። ስለ Exness ኮሚሽኖች በትሬዲንግ አካውንትዎች ክፍል በትሬድ ማድረግ የሚፈልጉት ገበያዎች ድረገጾች ላይ የበለጠ ይወቁ።
  • የሽያጭ እና የግዠ ስዋፕ - ስዋፕ በምሽት ክፍት ሆነው ለሚያድሩ የትሬዲንግ ግብይት አቋሞች ተግባራዊ የሚደረግ ወለድ ነው፣ እና በትሬዱ በመሰረት ሊገዛ ወይም ሊሸጥ ይችላል። የሽያጭ ስዋፕ የሽያጭ የግብይት አቋሞች ተመን ሲሆን የግዢ ስዋፕ ለግዢ የግብይት አቋሞች ተመን ነው። ስዋፑ በተለዋዋጭ ሁኔታ ሲለወጥ፣ በገበያ ሁኔታዎች መሰረት፣ የመጨረሻው ስዋፕ ሊለይ የሚችለው የግብይት አቋሙ በምሽት ክፍት ሆነ እንደቆየ በሚታሰብበት ወቅት ብቻ ነው። ስለ Exness ኮሚሽኖች በትሬዲንግ አካውንትዎች ክፍል በትሬድ ማድረግ የሚፈልጉት ገበያዎች ድረገጾች ላይ የበለጠ ይወቁ።
  • የፒፕ መጠን - ይህ የሚለየው የ1 ፒፕ መጠን ነው፣ ማለትም አንድ ትሬደር ምን ያህል ገንዘብ እንደሚያገኝ ፣ ወይም የትሬድ ዋጋ በአንድ ፒፕ የሚንቀሳቀስ ከሆነ፣ እንደሚከስር ለማስላት የሚረዳው ነው። የፒፕ መጠን የሚሰላው በአሀዶች x የውል መጠን xየፒፕ መጠን ፎርሙላ የምንዛሬ ዋጋ ነው። ሁሉም ውጤቶች የሚቀርቡት በትሬደሮች አካውንት ምንዛሬ ነው።

ትሬድ እያደረጉት ባለው መሳሪያ መሰረት ውጤቶች በቅርብ የእውነተኛ-ጊዜ የExness ልውውጥ ተመኖች በመጠቀም ሊተረጎሙ ይችላሉ።


የትሬዲንግስ ማስያ በሚጠቀሙበት ጊዜ፣ የቅድመ ዝግጅት ሌቨሬጅ ስላላቸው ለተወሰኑ መሳሪዎች ሌቨሬጅ አይገኝም። በእንደዚህ አይነት ሁኔታዎች ሌቨሬጅ ቋሚ ሲሆን፣ መቀየር አይችልም፣ እና በትሬዲንግ አካውንትዎ ላይ ባለው ሌቨሬጅ ተጽእኖ አያድርበትም።


ለምን Exness

ከገበያ-የተሻለ-ሁኔታዎች፣ ልዩ ባህሪያት እና ቆራጥነት-ያለው ደህንነት፣ ለግልጽነታችን እና የላቀ የደንበኞች አገልግሎት ከሰጠነው ቁርጠኝነት ጋር በመተባበር ትሬደሮች Exnessን መምረጣቸውን የሚቀጥሉበት ምክንያቶች ናቸው።

ፈጣን ወጪዎች

የእርስዎን ፈንዶች መቆጣጠርዎን ይቀጥሉ። በቀላሉ የሚፈልጉትን የክፍያ መንገድ ይምረጡ፣ የወጪ ጥያቄ ያቅርቡ፣ እና ቅጽበታዊ የራስ ሰር ማጽደቅን ያጣጥሙ።¹

እጅግ በጣም-ፈጣን አሰራር

ከፈጣን-አፈፃፀም ጋር ከአዝማሚያዎች ቀደም ብለው ይገኙ። የእርስዎን ትእዛዞች በሚሊሴኮንዶች ውስጥ በExness በሚገኙ ሁሉም መተግበሪያ መድረኮች ያስፈጽሙ።

የኪሳራ ከለላ

ልዩ የሆነውን የእኛን የኪሳራ ከለላ ባህሪይ ያጣጥሙ። መዘግየትን እና አንድ አንዴ ሙሉ ለሙሉ ከ Exness ጋር ትሬድ በሚያደርጉበት ወቅት ኪሳራዎችን ያስወግዱ።

የግብይት መንገድዎን ያሻሽሉ

ከ800,000 ትሬደሮች እና 64,000 አጋሮች በላይ ለምን Exnessን የብሮከር ምርጫ እንደሆነ ለራስዎ ይመልከቱ።